Fana: At a Speed of Life!

ብራዚል በኤክስ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱን አስታውቋል፡፡

በቢሊየነሩ ኤሎን መስክ የሚተዳደረው ኤክስ ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ የተነሳው ኩባንያው 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ በመክፈሉ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በሀገሪቱ የሚገኘው የኤክስ ቢሮ በብራዚል ዜጋ እንዲመራ ስምምነት ላይ መደረሱ ነው የተገለጸው፡፡

ኤክስ በፈረንጆቹ 2022 በብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ አሰራጭቷል በሚል በሀገሪቱ አገልግሎት እንዳይሰጥ መታገዱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.