Fana: At a Speed of Life!

የሊቨርፑል የቀድሞ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ እግር ኳስ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሬድቡል ኩባንያ ስር የሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች ሃላፊ መሆን የሚስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በሬድ ቡል ኩባንያ ስር በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀርመኑ ርቢ ሌብዢግ፣ የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ የአሜሪካው ኒውዮርክ ሬድ ቡልስ እና በብራዚል ደግሞ ሁለት እግር ኳስ ክለቦች ይተዳደራሉ፡፡

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በፈረንጆቹ 2025 ጥር ወር ጀምሮ ከላይ ለተጠቀሱት ክለቦች የበላይ አመራር ሆነው አንደሚሰሩ ሬደ ቡል ኩባንያ አስታውቋል፡፡

የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከሬድ ቡል ጋር የተፈራረሙት ስምምነት ከሊቨርፑል ጋር ከተለያዩ በኋላ የመጀመሪያ ቅጥራቸው ነው ተብሏል፡፡

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከመረሲሳይዱ ክለብ ጋር ፕሪሚየር ሊግ ፣ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችን ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.