Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ የስፔሻሊቲ ቡና ዐውደ-ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የጃፓን ስፔሻሊት ቡና ማኅበር ባዘጋጀው ዓለምአቀፍ የስፔሻሊቲ ቡና ዐውደ-ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

ዐውደ-ርዕዩን ያስጀመሩት በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ፣ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጃፓን ስፔሻሊቲ ቡና ማኅበር ፕሬዚዳት፣ የቡና ላኪ ሀገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በቶኪዮ ቢግ ሳይት ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የስፔሻሊቲ ቡና ዐውደ ርዕይ ላይ ኢትዮጵያ በስፋት እየተሳተፈች መሆኗን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ዳባ በዐውደ-ርዕዩ እየተሳተፉ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ቡና በማስገባት ላይ የሚገኙ የጃፓን ኩባንያዎችን አበረታትተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም አዳዲስ የጃፓን ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና እንዲያስገቡ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደርጓል ተብሏል፡፡

ዛሬ የተከፈተው ዐውደ-ርዕይ በፈረንጆቹ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2024 የሚቀጥል ሲሆን÷ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ቡና አምራቾች፣ ላኪዎችና ገዥዎች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.