Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ብልጽግና ፓርቲ ”የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡

በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና ከፌደራል እስከ ቀበሌ ደረጃ የሚገኙ 24 ሺህ 851 አመራሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት ያስችለዋል ተብሏል።

ስልጠናው ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ አመራሩ በአስተሳሰብ ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ ምግባር ጎልብቶ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም ያዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የሚቀጥለው ስልጠናው በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ የስልጠና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን÷ በመጀመሪያው ዙር ስልጠና የተሳተፉ አመራሮች በስልጠናው አስተባባሪነት ፣ በአስልጣኝነትና በአወያይነት የሚሳተፉ እንደሚሆን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.