የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆኜ ለማገልገል በመሰየሜ ክብር ይሰማኛል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አምስተኛው ፕሬዚዳንት ሆኜ ለማገልገል በመሰየሜ ክብር ይሰማኛል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ይህችን ታላቅና ተወዳጅ ሀገር እንዳገለገል ስለመረጡኝ ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ትናንት በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መሰየማቸው ይታወቃል።
አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማየቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡