አሜሪካዊያኑ በህክምና ዘርፍ የ2024 የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካዊያኑ ቪክቶር አምብሮስ እና ጋሪ ሩቭኩን መሰረታዊ የዘረ መል እንቅስቃሴ የሚመራበትን መሰረታዊ መርህ (ማይክሮ አር ኤን ኤ) በማግኘት የ2024 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል::
ባለሙያዎቹ በጋራ ያካሄዱት ጥናትና ምርምር በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እና ማሳቹሴትስ ሆስፒተል የተከናወነ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ግኝቱም መሰረታዊ የዘረ መል እድገት እና አሰራርን ማወቅ ያስቻለ ነው ተብሏል፡፡
የኖቤል አዘጋጅ ኮሚቴው ግኝቱ መሰረታዊ የዘረ መል እድገት እና አሰራርን ማወቅ በማስቻሉ ጠቃሚ ነው ብለውታል፡፡
ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ክትባትን በማግኘት የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የነበሩት አሜሪካዊያኑ ካታሊን ካሪኮ እና ድሪው ዌስማን መሆናቸው ይታወሳል፡፡
የ2024 የኖቤል አሸናፊዎች ዝርዝር በመጪዎቹ ቀናት በፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ስነ-ጽሁፍ እና በሌሎች ዘርፎች ይፋ እንድሚሆን ተነግሯል፡፡