Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው፤የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉ ብለዋል።

ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉ፤የሀገር ግንባታ የሚሳካውም በዚህ መንገድ ነው  ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ሃላፊነት የተቀበሉት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የሃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.