Fana: At a Speed of Life!

ብራዚል ቤቲንግን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላይ ብራዚል በኦንላይን የሚደረጉ የስፖርት ውርርድን (ቤቲንግ) ልታግድ እንደሆነ አስታወቀች፡፡

ውሳኔው በሀገሪቱ የሚደረጉ የስፖርት ውርርዶች ወደ ሱስነት በመቀየራቸው የተነሳ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች መከሰታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመግታትም ብራዚል በቤቲንግ ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን፤ ይህ እገዳ ውጤታማ ካልሆነ የስፖርት ውርርድን ከሀገሪቱ እንደምታግድ አስታውቃለች፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ትናንት በሳኦ ፖሎ ከተማ በሰጡት መግለጫ÷ የተጣለው እግድ ለውጥ ከሌለው የስፖርት ውርርድን ለማስቆም አናመነታም ብለዋል፡፡

ይህ የቁማር አይነት ባህሪ ያለው ቤቲንግ ከሱስ አልፎ ወደ በሽታነት ሳይቀየር ለማስቆም እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ባሏት ብራዚል ቤቲንግ በፈረንጆቹ ከ2018 ጀምሮ በሀገሪቱ ህጋዊነት ያገኘ ሲሆን በርካታ ዜጎች የስፖርት ውርርድን ያለምንም ክልከላ ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቤቲንግ በቤተሰብ ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው የተባለ ሲሆን፤ የቤቲንግ ተሳታፊ ሰዎችም በተለያየ መንገድ ዕዳ ውስጥ መዘፈቃቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.