Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የፖሊዮ ክትባት መሠጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመጀመሪያ ዙር የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ) መከላከያ ክትባት መሠጠት ጀምሯል፡፡

ዛሬ የተጀመረው ክትባት ከአሁን በፊት ለተከተቡም ሆነ ላልተከተቡ ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት እንደሚሠጥ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ አስረድተዋል፡፡

እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት በሚሰጠው በዚህ ክትባት በክልሉ ከ4 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

ክትባቱን ለመስጠት አስፈላጊው ግብዓት መቅረቡን አረጋግጠው÷ ሕጻናት ክትባቱን ያለምንም ችግር እንዲወስዱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ማኅበረሰቡ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.