በአፋር ክልልን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎችን ተመረጡ
በአፋር ክልልን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎችን ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የምክክር መድረክ ሲሳተፉ የነበሩ ባለድርሻ አካላት የክልሉን አጀንዳዎች የሚያደራጁ 25 ወኪሎችን መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል ከትላንት ጀምረው በቡድን ሲመካከሩ የነበሩ አምስቱ ባለድርሻ አካላት ከእያንዳንዳቸው አምስት ተወካዮችን በመምረጥ በድምሩ 25 ወኪሎችን የክልሉን አጀንዳ እንዲያደራጁ መርጠዋል ተብሏል።
ወኪሎቹ ከፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት አካላት፣ ከወረዳ ማህብረሰብ ተወካዮች፣ ከተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የሀይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከተለያዩ ማህበራትና ተቋማት ተሳታፊዎች የተመረጡ እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
እነዚህ የተመረጡ 25 ወኪሎች የአፋር ክልል አጀንዳዎችን አደራጅተውና አጠናቅረው ነገ በዋና መድረክ ካቀረቡ በኋላ ለኮሚሽኑ እንደሚያስረክቡ ተጠቁሟል።
የአፋር ክልል የምክክር መድረክ ካለፈው ማክሰኞ መስከረም 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰመራ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።