ሠራዊቱ ከግዳጁ ጎን ለጎን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሠራዊት የቀጣናውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየተወጣ ካለው ግዳጅ ጎን ለጎን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።
የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የጊቤ ማሰልጠኛ ለአራት ወራት በሁለት ዙር ያሰለጠናቸውን የሻምበል እና የሬጅመንት ታክቲካል አመራሮችን አስመርቋል።
ዕዙ ውስጣዊ አንድነት የሚያጠናክር የሠራዊት ግንባታ ስራዎች ላይ በማተኮር የሠራዊቱ አቅም በስልጠና እየገነባ እንደሚገኝ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገልጸዋል።
ሠራዊቱ የቀጥናው ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየተወጣ ካለው ግዳጅ ጎን ለጎን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው አክለው የተናገሩት።
በስልጠናው አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጠኞችም የሽልማት መርሐ-ግብር ተከናውኗል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የጅማ ዞን እና የጅማ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የሰላም እና ጸጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።
በወርቃፈራሁ ያለው