በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር እንዳሻው ጣሰው በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል፡፡
ሽልማቱ የተበረከተው “የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ሀሳብ በማረቆ ልዩ ወረዳ እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው የትምህርት ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
በዚህም በክልሉ በ8ኛ እና በ12 ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የገንዘብ፣የታብሌት የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች ፣ የትምህርት ጥራት እና የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻል ረገድ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ዩኒቨርሲቲዎች፣ኮሌጆች እንዲሁም ሌሎች ተቋማትም እውቅና ተሰጥቷል፡፡
እንዲሁም አንድ መጽሀፍ ለአንድ ተማሪ ንቅናቄ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዞኖች እና ዘርፉን ለደገፉ ባለሀብቶች ርዕሰ መስተዳድሩ ሽልማት ማበርከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡