Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻ ለማክበር ለተገኙ እንግዶች አባገዳዎች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ለማክበር በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ የተገኙ እንግዶችን አባገዳዎች እንዳመሰገኑ የቱለማ አባ ገዳ እና የአባገዳዎች ህብረት ፀሀፊ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ገለጹ።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በድምቀት እና በተሳካ ሁኔታ ተከብራል ሲሉ አመስግነዋል።

ነገ ኢሬቻ ሆረ አርሰዲ ሲከበር በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሀላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በዓሉን በከተማችን ለማክበር ከውጭ፣ ከሀገር ውስጥ የተለያዩ አቅጣጫዎች የመጣችሁ እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በዓሉ ያማረ እና የደመቀ እንዲሆን በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል።

በማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.