‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በአዲስ አበባ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ሆረ ፊንፊኔ’ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከበረ።
በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ወጣቶችን ጨምሮ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና ከሸገር ከተማ አሥተዳደር የመጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች በበዓሉ ላይ ታድመዋል፡፡
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ለፈጣሪ (አምላክ) ምሥጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም እንዲሆን የሚለምንበት በዓል ነው፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎችም የኦሮሞ ሕዝብን ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳትና ጭፈራዎች ታጅበው በድምቀት አክብረዋል።
በመላኩ ገድፍ