አቶ አሻድሊ ሃሰን ኢሬቻ በሀገር ግንባታ ሂደት የጎላ ፋይዳ አለው አሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 207 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ኅብረት በተግባር የሚገለጥበት ኢሬቻ ከበዓልነት ባለፈ በትውልድ እና በሀገር ግንባታ ሂደት የጎላ ፋይዳ አለው አሉ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳች መልዕክት÷ ፍቅር፣ ሠላም፣ ይቅርታ፣ አንድነት እና ኅብረት በተግባር የሚገለጡበት ኢሬቻ ከበዓልነት ባለፈ በትውልድ እና በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ እጅግ የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
በመሆኑም በኢሬቻ አስተምኅሮ መሠረት ቂምና ጥላቻን አስወግደን፣ ይቅርታንና ፍቅርን ተላብሰን፣ አንድነታችንን እና አብሮነታችንን አፅንተን÷ በኅብረት የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ በኅብረት ለማሳካት የምንተጋበት ዘመን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡
የኦሮሞ ወንድም እህቶቻችን በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንላችሁ ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡