Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻን ሚና ለትውልድ ማሸጋገር ይገባል- ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻን ጉልህ ሚና በመጠበቅ ለትውልድ ማሸጋገር እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ አስገነዘቡ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሯ ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት÷ ኢሬቻ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑ ባሻገር አንድነትን ያጎለብታል ብለዋል፡፡

ኢሬቻ አንድነት፣ ምስጋና፣ እርቅና ሠላም የሚንጸባረቅበት መሆኑን አብራርተው÷ የበዓሉን ዕሴት ለትውልድ ለማሸጋገር መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.