Fana: At a Speed of Life!

ለኢሬቻ በዓል ተጓዥ እንግዶች ከ1 ሺህ 457 በላይ ተሽከርካሪዎች ተዘጋጁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓጓዙ እንግዶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ከ1 ሺህ 457 በላይ ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ ተሳታፊዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷ በአዲስ አበባ በአምስቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶቡሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶቡሶች ተዘጋጅተዋል ብሏል፡፡

በቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም 150 ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር ለበዓሉ አገልግሎት የሚሰጡ 1 ሺህ 457 ተሽከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.