6ኛው የኢሬቻ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሥድስተኛው የኢሬቻ ፎረም አዲስ አበባ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡
በፎረሙ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል፡፡
ፎረሙ እየተካሄደ የሚገኘው “ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡
የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲንብሩ በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢሬቻን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢሬቻን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚከናወነው ሥራም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው እና ኦሊያድ አህመድ