ሩሲያ ዜጎቿን ከሊባኖስ ማስወጣት ጀመረች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የዲፕሎማቶቿን ቤተሰብ አባላት ልዩ በረራ በማድረግ ከሊባኖስ ቤሩት ማስወጣት መጀመሯን የአደጋ ጊዜ ሚኒስትሩ አሌክሳንደር ኩሬንኮቭ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ ዛሬ በተደረገ ዜጎችን ከሊባኖስ የማስወጣት ተግባር በመጀመሪያ በረራ 60 ሰዎች ሩሲያ ይገባሉ።
ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣቱ ሂደት የሚከናወነው በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መመሪያ ነው ሲሉ መግለጻቸውን የዘገበው ሬውተርስ ነው።
ለአንድ አመት ያህል በጋዛ ከሀማስ ጋር ስትዋጋ የቆየችው እስራኤል በሊባኖስ የሀማስ ቡድን ላይ በአየር እና በእግረኛ ጦሯ አማካኝነት እርምጃ እየወሰደች ይገኛል።
ሂዝቦላህ በበኩሉ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል በማስወንጨፍ ላይ ይገኛል።
እስራኤል የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስላሃን ከገደለች በኋላ የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባቱ ይታወቃል።