የአፋር ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች አጀንዳዎቻቸውን ለይተው አጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ የአፋር ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች አጀንዳዎቻቸውን ለይተው አጠናቅቀዋል፡፡
በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በመድረኩ ከሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ህብረተሰቡን ወክለው ሲወያዩ የቆዩት ከ800 በላይ ተሳታፊዎች በሀገር ደረጃ መግባባት ሊደረግባቸው ያስፈልጋል ያሏቸውን አጀንዳዎች በስፋት ተመካክረው ለይተዋል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በአደራ ተረክበው በቀጣይ ቀናት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚወያዩ 54 ወኪሎችንም መምረጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡