የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በይፋ ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በይፋ ስራ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል።
የትግበራ ኮሚቴው አግባብነት ያላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ እና የተቋማት ምክትል ኮሚሽነሮችን በውስጡ ያቀፈ አደረጃጀት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና የሙከራ ንግድ ማስፈፀሚያ እቅድ እና በረቂቅ ደረጃ እየተዘጋጀ የሚገኘውን የቀጣናውን ስትራቴጂ ዝግጅት ሂደት እንደሚገመገም አመላክተዋል።