Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በመምህራን የሚነሱ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ይሰራል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር መስራች ጉባዔ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ÷ መምህራን መብትና ግዴታቸውን አጣምረው ትምህርትን ለሀገር ግንባታ እንዲያገለግል በማሰብ ማህበሩን በማቋቋማቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመስራቱ መሻሻሎች መታየታቸውን አስታውሰው፤ የትምህርት ጉዳይ በሁሉም የህብረተለብ ክፍል ትብብር የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም የአንድ መፅሃፍ ለአንድ ተማሪ ስኬት ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል።

መምህር መሪን የሚያስተምር፣ ራዕይ ያለው ትውልድ የሚቀርፅ በመሆኑ ሁሌም ራሱን ማብቃት እንደሚጠቅበት ገልፀው፤ መምህር ሁሌ የሚያነብና የሚዘጋጅ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግስትም በመምህራን የሚነሱ ችግሮችን በመወያየት እና በመነጋገር ለመፍታት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩ በዲላ ከተማ በመከናወን ላይ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ዙሪያ ከዞንና ከከተማ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት የክልሉን ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ አረንጓዴና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.