Fana: At a Speed of Life!

በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያተኮረ መድረክ በሆሳዕና እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የየክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ሃላፊዎችና የክልሉ የካቢኔ አባላት ተገኝተዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ክልሉን በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ ያለውን ጸጋ በመጠቀም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ማነቃቃት፣ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ማሟላት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ መጠቀሱንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.