Fana: At a Speed of Life!

በሊባኖስ  ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየሠራ መሆኑን ብሔራዊ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት በሊባኖስ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ የደኀንነት ሥጋት ያለባቸው ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚሁ ወቅት ሰብሳቢዋ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት እያደረገ ያለው ምዝገባ በሰው ኃይል እና በቴክኖሎጂ ታግዞ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቀዋል፡፡

ኮሚቴው በሊባኖስ ወቅታዊ ሁኔታ ደኀንነታቸው ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን አማራጮችን ሁሉ በመጠቀም ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ  ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ሥራውን በተሻለ ፍጥነት ማሳለጥ እንዲቻልም ተጨማሪ የሰው ኃይል ወደ ቤይሩት እንደሚላክ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.