ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ሚኒስትሯ÷ የሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ መንግስት እያደረገ ስላለው ጥረትና ተቋማቸው እያከናወነ ስላለው ሥራ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡
ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ማህበሩ የጀመረውን ሥራ አድንቀው በቀጣይ ሚኒስቴሩ በሥራ ፈጠራው መስክ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከማህበሩ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የማህበሩ መስራችና ፕሬዚዳንት ሳሚያ አብዱልቃድር÷ የማህበሩን የቀጣይ ዓመታት ስትራቴጂክ ሰነድ ለሚኒስቴሩ አስረክበዋል፡፡