Fana: At a Speed of Life!

ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ በሊባኖስ የሚገኙ ዜጎች ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በተከሰተው ውጥረት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀረበ፡፡

በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጄነራል ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ÷ በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ከሊባኖስ መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ እና እስከ አሁን ያልተመዘገቡ ወገኖች አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎችም÷ ሙሉ ስም ከነአያት(ፓስፓርት ላይ እንደተፃፈው)፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ በሊባኖስ የቆይታ ጊዜ፣ የሊባኖስ ስልክ ቁጥር መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

ለምዝገባ የተዘጋጁት ስልክ ቁጥሮችም÷ 03-29-89-78፣ 76-03-08-23፣ 81-99-46-34፣ 70-29-80-91፣ 81-80-25-18፣ 70-84-25-24 እና 81-09-27-46 መሆናቸውን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ቀደም ሲያል ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተመዘገቡና መመዝገባቸውን ያረጋገጡ ወገኖች በድጋሚ እንዳይመዘገቡ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.