እስራኤል የተመድ ዋና ጸሐፊ ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ ወደ ግዛቴ እንዳይገቡ ስትል እገዳ መጣሏን አስታወቀች።
ሀገሪቱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈችው ዋና ጸሀፊው ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤል ማስወንጨፏን ተከትሎ ድርጊቷን አላወገዙም በሚል መነሻነት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ ኢራን የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የተመድ ዋና ጸሐፊ አለማውገዛቸው እገዳው እንዲጣል ማድረጉን ገልጸዋል።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በሊባኖስ እየደረሰ ያለውን ቀውስ ጠቅሰው ችግሩ እንዳይስፋፋ የተኩስ አቁም መደረግ እንዳለበት ማሳሰባቸው ይታወቃል።