ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት እደግፋለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ሂደት በፋይናንስና በቴክኒክ እንደሚደግፍ አረጋገጠ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት አብራርተዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ጥረት ሊደግፍ የሚችልባቸውን ጉዳዮች አመላክተው÷ ሂደቱ የሚቀላጠፍበት ሁኔታ እንዲፈጠር እግዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ጥረትና ሂደት ባንኩ በፋይናንስና በቴክኒክ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡