Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የምልክት ቋንቋ ጉባዔ ድጋፍ አደርጋለሁ- ተመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምታስተናግደው 15ኛው ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባዔ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ጸሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ራሚዝ አልካባሮቭ (ዶ/ር) ጉባዔውን በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ጉባዔው በያዝነው ዓመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራትና ተቋማት የተወጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት ለሚጠበቀው ጉባዔም÷ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሀብት ማሰባሰብ ሥራ እንደሚከናወን መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ራሚዝ አልካባሮቭ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ ይህን ትልቅ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ለማስተናገድ የወሰደችውን ተልዕኮ አድንቀው÷ ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.