በመዲናዋ ከሁሉም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ሰልጣኝ የሠላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ያሰለጠናቸው የሠላም ሰራዊት አባላት ዛሬ ተመረቁ።
ተመራቂዎቹ የሠላም ሠራዊት አባላትና አመራሮች የንድፈ ሃሳብና የመስክ ሥልጠና የወሰዱ ሲሆን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ናቸው ተብሏል።
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸነር ጌቱ አርጋውን ጨምሮ የከተማ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።