Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እየሠራች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየሠራች መሆኗን በኢትዮጰያ የሀገሪቱ አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ አስታወቁ፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ከኢኮኖሚያዊ መስኮች ባሻገር በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ጭምር ለማጠናከር እየተሠራ መሆኑንም ነው አምባሳደሩ ያስረዱት፡፡

በዚህም ጣሊያን በአንድ ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ከ300 ሚሊየን ዩሮ በላይ ድጋፍ ማድረጓን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለጣሊያን ስትራቴጂክ አጋር ከሚባሉት ሀገራት አንዷመሆኗን ጠቅሰው÷ በቀጣይ የትብብር መስኮችን በማጠናከር ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየሠራች ነው ብለዋል፡፡

በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም የባለ ብዙወገን ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚሠሩ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.