በአማራ ክልል 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ደብተር ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አባይ ሕትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ በአማራ ክልል በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ትምህርት መከታተል ላልቻሉ ተማሪዎች 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያውጣ ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተረክበዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ፋብሪካው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ፈታኝ በሆነበት ወቅት ድጋፍ በማድረጉ ድርጅቱንና አመራሮችን አመስግነዋል፡፡
ቢሮው በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆኑ ከተለያዩ አጋር አካላት የትምህርት ግብዓቶችን እያሰባሰበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶችም የመማሪያ ግብዓቶችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡