የሸካቾ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸካቾ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ‘ማሽቃሬ ባሮ’ በዓል በጌጫ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የ ‘ማሽቃሬ ባሮ’ በዓል በተለያዩ ምክንያቶች መከበር ከተቋረጠ ከ146 ዓመት በኋላ ዘንድሮ እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ ያለፈውን ዘመን በመሸኘት አዲሱን ዘመን ለተሻለ ስኬት በአዲስ መንፈስ በመቀበል የሚከበር መሆኑን የብሔረሰቡ ባህል አዋቂዎች ተናግረዋል።
በበዓሉ የብሔረሰቡ ተወላጆች፣ የአጎራባች ዞኖች ነዋሪዎች እንዲሁም የክልልና የፌደራል ተቋማት እንግዶች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በተስፋየ ምሬሳ