Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የኮደርስ ስልጠና በተደራጀ አግባብ እየተሰጠ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የኮደርስ ስልጠና በተደራጀ አግባብ እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

አቶ ኦርዲን እንዳሉት÷የኮደርስ ስልጠና በርካታ ዜጎች በቴክኖሎጂ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ያለንበት ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን በመሆኑ ወጣቱ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሳተፍ ለማድረግ ስልጠናው አይተኬ ሚና አለው ብለዋል።

በሐረሪ ክልል በርካታ ወጣቶች የሚገኙ በመሆኑ እነዚህ ወጣቶች የስልጠናው ተሳታፊ እንዲሆኑ በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰዋል።

በክልሉ ትምህርት ተቋማት በክረምት ወራት ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በዚህ ስልጠና ላይ እንዲያሳልፉ መደረጉን ተናግረዋል።

በክልሉ በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ሁሉም ዜጎች ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ ያሉ ወጣቶች በቴክኖሎጂ ብቁ ሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በአዲሱ በጀት ዓመት በልዩ ትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

ስልጠናው የወጣቶችን ቴክኖሎጂ አቅም ከመገንባት ባሻገር ሀገር ለምታደርገው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አቅም እንደሚሆን ለኢዜአ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.