Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል ተጨማሪ የሂዝቦላህ ከፍተኛ አመራር መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት ተጨማሪ የሂዝቦላህ ከፍተኛ አመራር መግደሏን አስታውቃለች፡፡

በሊባኖስ በመሸገው ሂዝቦላህ ላይ የሚወሰደው ሁለንተናዊ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለትም በቤሩት በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ የተሳካ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጦሩ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡

በዚህም የሂዝቦላህ ደህንነት ሃላፊና የማዕከላዊ ም/ቤቱ ወሳኝ አባል ነቢል ኳዑክ መገደሉን ነው ያስታወቀው፡፡

በአንጻሩ በከፍተኛ አመራሩ መገደል ዙሪያ ሂዝቦላህ ያለው ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ እየወሰደች ባለው ወታደራዊ እርምጃ የቡድኑን መሪ ሀሰን ነስራላህን ባሳለፍነው አርብ መግደሏ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.