Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)ና የገቢዎች ሚኒስትር አይናም ወይዘሮ ንጉሴ ተሳትፈዋል፡፡

ጉብኝቱን አስመልክቶ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”እንኳን ወደ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በሰላም መጣቹሁ፤ የእረፍት ቀናቹሁን ሰውታቹሁ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ስራዎቻችንን ስለጎበኛችሁ እጅግ እናመሰግናለን” ብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.