Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በኢሜሬትስ ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው አርሰናል 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፏል፡፡

ለአርሰናል ሊያንድሮ ትሮሳርድ(ሁለት) እና ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ካይ ሀቨርትዝ ሲያስቆጥሩ የሌስተር ሲቲን ሁለት ጎሎች ጄምስ ጀስቲን አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ የኤንዞ ማሬስካ ቡድን ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ብራይተንን አስተናግዶ 4 ለ 2 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው የቼልሲው የፊት መስመር ተጫዋች ኮል ፓልመር በ10 ደቂቃ ሀትሪክ መስራት የቻለ ሲሆን ÷በጨዋታው በ40 ደቂቃ ውስጥ የቼልሲን አራት ጎሎች ማስቆጠር ችሏል፡፡

የብራይተንን ጎሎች ደግሞ  ጀርጊኒዮ ሩተር እና ካርሎስ ባሌባ አስቆጥረዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 ፤ፉልሃም ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ  ዌስትሃም እና ብረንትፎርድ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.