እስራኤል የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስራላህን መግደሏን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው እስራኤል የቡድኑን መሪ ሀሰን ነስራላህን መግደሏን አስታውቃለች።
የእስራኤል መከላከያ ሃይል እንደገለጸው፤ ሀሰን ነስራላህ ቤይሩት ውስጥ በአርብ ምሽት ጥቃት ተገድለዋል።
ሂዝቦላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ያለው ነገር አለመኖሩን የገለጸው የቢቢሲ ዘገባ፤ የእስራኤል የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ እንደሆነ ገልጿል።
የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ቤይሩት እየፈጸመ ያለው ጥቃት በተመረጡ ኢላማዎች ላይ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።
የሊባኖስ ባለስልጣናት በበኩላቸው እስራኤል ጥቃት መፈጸም ከጀመረችበት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ 800 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።