Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ፍቅራችንና አንድነታችን በማጎልበትና በመደጋገፍ ልናከብረው ይገባል – ከንቲባ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከበር ፍቅራችንንና አንድነታችንን በማጎልበትና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

ከንቲባው የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ የመስቀል ደመራ በዓል በአደባባይ ከሚከበሩ ድንቅ እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከተቀዳጁ በዓላት መካከል አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

በዓሉን ስናከበር የእርስ በርስ ፍቅራችንንና አንድነታችንን፤ በጋራ የጋራ ማህበራዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ለመሻገር የጀመርናቸውን ተግባራት በማጠናከር መሆን አለበት ብለዋል።

በዓሉን ስናከበር በዘንድሮ አመት የተወጡኑትም የሰላም እና የልማት ስራዎች ዳር ለማድረስ በመነሳሳት መሆን እንዳለበት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.