Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡

ሁሉም የጸጥታ አካላትም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ በበኩላቸው÷ በዓሉን በሰላም ለማሳለፍ የሚፈልግ በርካታ ሕዝብ እንዳለ ሁሉ የበዓሉን ድባብ ለማጠልሸት የሚንቀሳቀስ አካል እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡

በዚሁ መሠረት እስከ አሁን የአሸባሪው ሸኔ፣ የፅንፈኛው ቡድን፣ የአይ ኤስ እና የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ማለታቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.