በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሟቾች በተጨማሪ በ19 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፋታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡
የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው