Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከነገ እስከ ዓርብ ማለዳ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ማለዳ 12 ሠዓት እስከ ዓርብ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ እንዳስታወቀው÷ ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል ከመስከረም 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ በመዲናዋ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት ተከልክሏል፡፡

የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ቢሮው አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.