Fana: At a Speed of Life!

99 ኢትዮጵውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 99 ህገ ወጥ ፍልሰተኞች ከነጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን ገለፀ።

ዜጎቹን የመመለሱ ስራ ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

ኤምባሲው በየጊዜው ፍልሰተኞች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እየሰራ ቢሆንም በህገ-ወጥ ስደት ምክንያት በየቀኑ የሚጠፋውን የሞት ቁጥር መቀነስ አለመቻሉን አስገንዝቧል።

ስለሆነም ይህ ስራ የዜጎችን ውሳኔ እና የተቋማት የጋራ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለዚህ ተግባር እንዲተባበር በመጠየቅ ኤምባሲው ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.