Fana: At a Speed of Life!

ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በገበታ ለሀገር ከተገነቡ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አንዱ – ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት

👉 ፕሮጀክቱ ከወሊሶ አምቦ፤ ከወንጪ ደንዲ፤ ከደንዲ አስጎሪ ሰፊ የሆነ ቦታ ላይ በምዕራፍ ተከፋፍሎ እንዲገነባ የተቀረጸ ሰፊ ራዕይ ያለው ትልቅ ሀገራዊ የልማት ዐሻራ ነው፡፡

👉 የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቋል።

👉 በግንባታ ሂደት ብቻ ከ10 ሺህ ለሚበልጡ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

👉 ፕሮጀክቱ ከቱሪስት መዳረሻነት ባሻገር ለአካባቢው የማያቋረጥ የሥራ ዕድልና ልማት ማስገኘቱን ይቀጥላል፡፡ ለአብነትም በ22 ማኅበራት ለተደራጁ ከ560 የሚበልጡ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ መሠራቱ ይታወቃል፡፡

👉 ከአዲስ አበባ 135 ኪሎ ሜትር ርቀት ከወሊሶ-አምቦ መንገድ መሃል ላይ በእሳተ ጎመራ የተፈጠረ ነው፡፡

👉 ወንጪ ሐይቅ ዙሪያ ገባውን አረንጓዴ በለበሱ ድንቅ ተራራዎች የተከበበ ውብ ስፍራ ነው።

👉 በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተተከለውን ታሪካዊና ጥንታዊውን ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ያቀፈው ዝምተኛው ወንጪ ሐይቅ÷ ከእምቅ የብዝኃ-ሕይወት ባለቤትነቱ ባሻገር ለአካባቢው ነዋሪዎች ለመጠጥነት ይውላል።

👉 ይህ ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት የ2021 ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሽልማትን አሸንፎ በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደው የዓለም ቱሪዝም ድርጅት 24ኛ ጠቅላላ ጉባዔ መድረክ ላይ ሽልማቱ በይፋ ተሰጥቷል፡፡

👉 ባህላዊና ተፈጥሯዊ ጸጋዎችን የታደለው ወንጪ ሐይቅ የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር መሰኘቱ ለዘላቂ የቱሪዝም ልማትና ተጠቃሚነት ፋይዳው ጉልህ እንደሆነም ይነገራል፡፡

👉 ሽልማቱ ለሌሎች ማኅበረሰብ አቀፍ ቱሪዝም ልማት እንቅስቃሴዎች ተምሳሌትና ብርታት እንደሚሆን፤ እንደ ሀገርም መንግሥት በቱሪዝም ልማት ረገድ ትክክለኛ መንገድ ላይ ለመሆኑ ማሳያ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.