Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከል ግንባታ ተጠናቅቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ እንደገለጹት÷የማዕከሉ ሥራ መጀመር አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ የሚባክነውን ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ሥራ እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።

የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንት በሃይሉ መርደክዮስ በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው ዘመኑን የዋጀ ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል ።

በተመሳሳይ የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከሉ የናሙና መቀበያ ግንባታ ተጠናቅቆ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትሕ አካላት ጋር በመቀናጀት ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.