Fana: At a Speed of Life!

ውጤታማ የተግባቦት ሥራን ማሳደግ ይገባል- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ውጤታማ የተግባቦት ሥራን በቀጣይነት በማሳደግ በመንግሥት ፖሊሲዎችና ሥራዎች ላይ ለኅብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስገነዘበ፡፡

በጽሕፈት ቤቱ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል በተለያዩ ሚኒስቴሮች የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን ያሰባሰበ የመንግሥት የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን ለማላቅ ይቻል ዘንድ በ ”ዘመናዊ ኮሙኒኬሽን” ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው በመለወጥ ላይ የሚገኘውን የዓለም እና የሀገራችን የኮሙኒኬሽን ዐውድ ተገንዝቦ ስለመንግሥት ፖሊሲዎች፣ አገልግሎቶች እና ቁልፍ ሥራዎች ጠቃሚ መረጃዎችን በወቅቱ ማቅረብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለሰፊው ተደራሲ የሕግ ማዕቀፎችን እና በሕጎቹ የመመራት መሥፈርቶችን ግልፅ ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

ውጤታማ የተግባቦት ሥራን በቀጣይነት በማሳደግ በመንግሥት ፖሊሲዎች እና የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በኅብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

እነዚህ ጥረቶች መረጃ ያለው እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ዜጋ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ብሎም መንግሥት ለግልፅነት ያለውን ፅኑ አቋም የሚደግፉ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.