የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።
ስሁል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ባህር ዳር ከነማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፥ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በተመሳሳይ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ወደ ሀድያ ሆሳዕና አቅንቶ እንግዳውን ወልቂጤ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
በሌላ በኩል ድሬ ዳዋ ከተማ ከሃድያ ሆሳዕና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድሬ ዳዋ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ጨዋታው ነገ ቀጥሎ ሲካሄድ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለማቀፍ ስታዲየም መቀሌ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታል፤ ጅማ አባ ጅፋር እና ሲዳማ ቡና ደግሞ በአደማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።