በአማራ ክልል በ13 ሺህ 683 ሄክታር ላይ ምርጥ ዘር እየለማ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2016/17 ምርት ዘመን በ13 ሽህ 683 ሄክታር መሬት ላይ የተለያየ ዓይነት ሰብል ምርጥ ዘር እየለማ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በክልሉ የምርጥ ዘር ፍላጎትን በራስ አቅም ለማሟላት በተከናወነው ሥራ ተስፋ ሰጭ ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
በቀሪ ቀናት የሰብል እንክብካቤ የበሽታና የተባይ አሰሳ በማድረግ ጥራት ያለው ዘር ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ በትኩረት እንደሚሰራ መጠቆሙንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡