የጋሞ ዞን ሕዝቦች የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚዬም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ”ዮ ማስቃላ” ፣ ”ቡዶ ኬሶ” እና ”ባላ ካዳቤ” የጋሞ ዞን ሕዝቦች የዘመን መለወጫ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚዬም በአርባምንጭ እየተካሄደ ነው፡፡
ሲምፖዚዬም ”ዱቡሻና ዱቡሻ ዎጋ ለዘላቂ ሠላማችን እና ልማታችን በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በሲምፖዚዬሙ በ”ዮ ማስቃላ” ፣ ”ቡዶ ኬሶ” እና ”ባላ ካዳቤ” በዓላት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
ዱቡሻና ዱቡሻ ዎጋን በዩኔስኮ በማይዳሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሆነ መገለጹንም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በባሕልና የቋንቋ ሲምፖዚዬሙ የፌደራል ፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ምሁራን እና የአካባቢው ተወላጆች ተሳትፈዋል፡፡