Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው ለ”መሣላ”በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ለከምባታ ዞን ሕዝቦች ዘመን መለወጫ”መሣላ”በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷የ”መሣላ”በዓል ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር፣ መንፈስን በማደስ ነገን ብሩህ ለማድረግና ለመትጋት መነሳሳትን የምንጎናፀፍበት ነው ብለለዋል፡፡

ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ብሔሮችና ብሔረሰቦች የማንነታቸውን መገለጫዎች አንዲንከባከቡና እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አንስተዋል፡፡

የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ለተጀመረው ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ አጋዥ አቅም አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የማንነት መገለጫዎችን ከማሳደግ ጎን ለጎን ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን የሚያፀና የጋራ ትርክትን ማጠናከር ከመላው ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ የጋራ ሃላፊነት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.